
በቂርቆስ ክ/ከተማ እየተካሄደ ያለዉ የአቅመ ደካሞች የመኖርያ ቤት ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ የመስክ ምልከታ ተካሄደ
ITDB፦ ግንቦት 1/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ መስጂድ ጀርባ በሚባል አካባቢ ለአስራ ሁለት አባወራ የሚሆን G+2 መኖርያ ቤት ግንባታ ማስጀመሩ ይታወሳል። በመሆኑም የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ፣ ምክትል የቢሮ ሀላፊዎችና ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የቄርቆስ ክ/ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎ በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ጽ/ቤት ሀላፊ በተገኙበት የቤቱ ግንባታ ያለበት ደረጃ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።
በምልከታ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ ቢሮዉ በቀጣይ መከናወን ስላለበት ተግባርና እንዲሁም ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ቤቶችን በአጭር ግዜ ዉስጥ እንደሚያጠናቀቅና ለዚህም መሳካት አመራሩ ከፍተኛ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።
የግንባታ ስራዉን የሚያከናዉነዉ ጉሽ ኮንስትራክሽን 180ካሬ ላይ ያረፈ የራሱ መፀዳጃ ቤት፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ስፍራ እና መኪና ማቆምያ ያለዉ ለ12 አባወራ የሚሆን G+2 መኖርያ ቤት ግንባታ 45 በመቶ መጠናቀቁንና ቀሪዉን 55 በመቶ በአጭር ቀናት ዉስጥ ግንባታዉን በማጠናቀቅ ርክክብ እንደሚያካሂዱ ገልፀዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments