
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት ተካሄደ።
ITDB፦ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም
በመርሃ-ግብሩ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት እና የወረዳ እንዲሁም የሴክተር መስርያ ቤት አመራሮች ተገኝተዉበታል።
መርሃ ግብሩን የመሩት የቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ግሩም አብተዉ የመርሃ-ግብሩ ዓላማ ያለፈዉን ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የምንገመግምበትና ቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን የምንለዋወጥበት እንዲሁም ከማዕከል፣ ጽ/ቤት እስከ ወረዳ ተነባቢ የሆነ ዕቅድ ሪፖርት እንዲኖር ማስቻል መሆኑን ገልፀው ከዚህም ባሻገር አዳዲስ የመጡ የቢሮ አመራሮች ጋር ትዉዉቅ ማድረግ መሆኑን አመላክተዋል።
በተያያዘም የመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸዉን አስተላፈዉ ቢሮዉ የተቋቋመበት ዓላማና በዛሬዉ መርሃ-ግብር አምስት ትልልቅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዉይይት እንደሚካሄድና ከነዚህም መካከል፦ ስልታዊና ተናባቢ ዕቅድ እንዲኖር ማስቻል፣ ችግር ፈቺና ፈጠራ የታከለበት የጋራ ስራ መስራት ላይ፣ በሳይበር ደህንነትና ተጋላጭነት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ምንድናቸው መፍትሔዎቹ ላይ፣ የአቅም ግንባታ ስራን በተመለከተ እና ፖሊሲና የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ዉይይት እንደሚካሄድ በማመላከት መልካም የቆይታ ግዜ ተመኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮ ዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አርብሴ ቢሮዉ በ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የነበሩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶችን እንዲሁም የስትራቴጂክ ዕቅዶችን መነሻ በማድረግ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በማቀድ በመተግበር ላይ መሆኑን ገልፀው የቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም አቅርበዋል። በሪፖርቱም የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈፃፀም፣ የታዩ ጥንካሬ እና ክፍተቶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተሰጡ መፍትሔዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በዝርዝር ተዳሰዋል።
የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ሀላፊ እና ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብና አተገባበር፣ የስማርት ሲቲ ስድስት ምሶሶዎች፣ የስማርት ሲቲ የስምንት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላንና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ዕቅድን በጋራ ማሳካት ላይ በምሳሌ የተደገፈ ግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
በቀረበው ዕቅድ እና የስማርት ሲቲ ፅንሰ ሀሳብና አተገባበር ላይ መሰረት ያደረገ ዉይይት በቢሮ
ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድ እና ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን አማካኝነት ዉይይት የተካሄደ ሲሆን በዉይይቱም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል። ከነዚህም መካከል ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከበፊቱ የተሻለ ተግባቦት እንደተፈጠረና የስማርት ሲቲ ስድስት ምሶሶዎች በክ/ከተማ ደረጃ ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን አመላክተዉ ጽ/ቤቶች በራሳቸው አቅም እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ የተለያዩ ድጋፍ እንደሚሹ ተገልፅዋል፣ ሲስተሞችን ለዉጭ አካል ከመስጠት ይልቅ ያለዉን የሰዉ ሀይል በአግባብ በመጠቀም በዉስጥ አካል የማልማት ስራ ቢከናወን፣ ተቋምን ከማጠናከር አንፃር ግልፅ የሆነ አደረጃጀት መፍጠር ቢቻል፣ የሰራተኞች ፍልሰት ከመከላከል አንፃር ደሞዝና ጥቅማጥቅም ላይ ማስተካከያ ቢደረግ የሚሉ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን የተነሱ ሀሳብ አስተያየቶችን እንደግብዓት በመዉሰድ አወያዬች ምላሽ ስጥተዉበታል።
በመጨረሻም በቢሮ ሀላፊ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የተቀመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የፈጠራ ስራ መስራት የሚችሉ አቅም ያላቸዉ ህብረተሰብ ክፍል ለማፍራት ያስችለን ዘንድ እንደ ከተማ የICT professional network platform ሊኖረን እንደሚገባ፣ የአቅም ግንባታ ስራ ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት እንደሚገባ፣ ክ/ከተማና ወረዳዎች በማወዳደር ተሞክሮዎችን ማስፋትና ልዩነቶችን ለማጥበቡ እንደሚገባ፣ ድጋፍና ክትትልን በተመለከተ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም አመርቂ ዉጤት ማምጣት እንደሚገባና የፈጠራ ስራዎች ጎልተዉ እንዲወጡ የበኩላችንን እንወጣ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments