የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክ...

image description
- In Technology Trends    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ የለማው የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ሲስተም የሙከራ ትግበራ ማድረግ ላይ ምክክር ተካሄደ።

ITDB፦ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ የለማው የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ሲስተም ላይ የቢሮ ሀላፊ አቶ አዋሌ መሀመድና ስትራቴጂክ ካዉንስል አባላት እንዲሁም ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክብርት ልዕልት ግደይ በተገኙበት የሙከራ ትግበራ ማድረግ የሚያስችል ምክክር አካሄዱ።

የለማው ቴክኖሎጅ አገልግሎት አሰጣጡንና አሠራሩን ከማዘመን ባለፈ የህዝብ ሀብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉንና አለመዋሉም የሚረጋገጥበት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አዋሌ መሐመድ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት በከተማዋ ለሚገኙ የመንግስት ተቋማት ቴክኖሎጅ በማልማት ራዕያቸውን እንዲያሳኩ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን የለማውን ቴክኖሎጅ እንደ አስፈለጊነቱ በሁለቱ ተቋማት ስምምነት መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ የእርምት ይወሰዳልም ብለዋል።

ክብርት ኮሚሽነር ልእልት ግደይ ኮሚሽኑ በሪፎርም ትግበራው ከለያቸው ትግባራት አንዱ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ቴክኖሎጅ እንዲያለማ በከተማ አስተዳደሩ ስልጣንና ተግባር ከተሰጠው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል። አክለዉም በቀጣይም እንደ አስፈላጊነቱ ቴክኖሎጂ ማልማትና በተመሳሳይ ጉዳዮች በቅንጅት መስራቱን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳላቸዉ አመላክተዋል።

በመጨረሻም የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም ካደረጉ 16ቱ ተቋማት አንዱ እንደ መሆኑ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ፈጣንና ቀልጣፋ ፍትሀዊ አገልግሎት ለመስጠት ቢሮዉ የቀረበለትን የቴክኖሎጂ ይልማልን ጥያቄ ተቀብሎ ምላሽ በመስጠቱ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB

ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et

መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments