የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክ...

image description
- In Entertainment    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከሚያካሂዳቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከሚያካሂዳቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጡ ለማድረግ ሲስተሞችን በማዘመን ወደ ተግባር ማስገባትና ተፈጻሚነታቸውን መከታተልና ድጋፍ ማደረግ ነው፡ከነዚህም ውስጥ ለአዲስ አበባ ከተማ ከነማ ፋርማሲዎች በቴክ-ኢትዮ አይሲቲ ሶሉሽን የለማው የኢ.አ.ር.ፒ ሲስተም (ERP System) አንዱ ሲሆን የለማውን ሲስተም ወደ ተግባር እንዲገባ በተለያዩ ጊዚያት የሚመለከታቸው የከተማው ቢሮዎችና ጽ/ቤቶች (አዲስ አበባ ከተማ ስራ እስኪያጅ ጽ/ቤት ፣ ከነማ ፋርማሲዎች  ድርጅት ፣ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና አዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ) የበላይ አመራሮች በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የበለጸገው የኢ.አ ር.ፒ ሲስተም (ERP System) ከነማ ፋርማሲ ለከተማ ነዋሪዎች ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንጻር አስፈላጊ በመሆኑ ከአልሚ ድርጅቱም ጋር ውይይቶችን በማካሄድ ሲስተሙ ወደ ትግበራ የሚገባበት መንገድ እንዲመቻች በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ቢሮው ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ብዛታቸው 69 ለሆኑ ለከነማ ፋርማሲ ባለሙያዎች ስልጠናው ከሰኔ 10እስከ 21 ድረስ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments