The Addis Ababa City Administr...

image description
- In Training    0

The Addis Ababa City Administration Innovation Technology Development Office has completed preparation for civil registration and residential service system.

                                                                      

የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ መረጃ ለማደራጀት የሚያስችል ኢትዮ ኮደርስ ማኔጅመንት ሲስተም ወደ አገልግሎት ገብቷል
**** 

ITDB፦ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል። ከነዚህም ተግባራት መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው አምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ላይ ማህበረሰብን ተሳታፊ ከማድረግ አንፃር በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል። 

በመሆኑም በዛሬው ዕለት የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ አራት ኮርሶች፦ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ አንድሮይድ ዲቨሎፕመንት፣ ፕሮግራሚንግና ዳታ አናላይስስ የወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ለማደራጀት የሚያስችል ኢትዮ ኮደርስ ማኔጅመንት ሲስተም ወደ አገልግሎት አስገብቷል። 

በዚህ ሲስተም አተገባበር ዙርያ የ11ዱ ክ/ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊዎች አስተባባሪና ቡድን መሪዎች፣ ትምህርት ቢሮ፣ ስራና ክህሎት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የፐብሊክ ሰርቪስ አይቲ ዳይሬክተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ተቋማቱን ወደ ሲስተሙ የማስባት ተግባር  ተከናውኗል። 

ይህንን ሲስተም በመጠቀም ምን ምን ተግባራትን ማከናወን እንደሚቻል በአልሚዉ ድርጅት ማብራርያ የተሰጠ ሲሆን የቢሮ ስማርት ሲቲ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቱሉ ጥላሁን በዚህ ሲስተም አማካኝነት በየተቋማቱ ኢትዩ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ ስንት መድረክ እንደተፈጠረ፣ ምን ያህል ሰዉ እንደተሳተፈ፣ የዕቅድና ሪፖርት ልዮነት እንዳይፈጠር፣ አፈፃፀም እንዲጨምርና የጠራ መረጃን በቁጥርና በፆታ እና ለመያዝ እንደሚጠቅም ገልፀዉ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። 

ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et   ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments