
ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የመጡት ቴክኒካል ቲሞች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ
ITDB፦ ሰኔ 19/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ ፐብሊክ ሰርቪስና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተወጣጡ ቴክኒካል ቲሞች በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዙሪያ የልምድ ልዉዉጥ አካሄዱ።
በልምድ ልውውጥ ስነ ስርዓት ላይ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዮናስ ደምሰው የአዲስ መሶብ አገልግሎት ምንነት፣ ዓላማው፣ ወደ አገልግሎቱ ስለሚገቡት የመጀመሪያዎቹ 13ቱ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት ስለሚሰሩት ተግባር፣ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎች አደረጃጀት፣ ስራው በታቀደለት መርሃ ግብር እየተከናወነ ስለመሆኑና የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት በዝርዝር አስረድተዋል። በተጨማሪም በስራው ሂደት ሊከሰቱ ስለሚችሉ ችግሮች እና መወሰድ ስለሚገባቸው መፍትሔዎች፣ የተሰሩ ስራዎች በተዘጋጀላቸው check list ክትትል እንደሚደረግባችው ገልፀዋል። በተደረገው ገለፃ ላይ መሰረት ያደረገ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አቶ ዮናስ ደምሰው እና ወ/ት ሙሉ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments