
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በዛሬዉ ዕለት በበይነ መረብ በተሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመፈተኛ ጣቢያዎች የኢንተርኔት እና ሌሎች ለፈተና የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች በአግባቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ በማከናወን ላይ ነዉ
ITDB፦ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም
በዛሬው እለት በተሰጠው የሙከራ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማትና የትምህርት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ሴክተር ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያው በመገኘት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን በዛሬው እለት የተሰጠው የሙከራ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ከየፈተና ጣቢያው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
የዛሬው የሙከራ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው መደበኛ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የሙከራ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው የሙከራ ፈተና ፈተናውን በበይነ መረብ ለመስጠት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተዘጋጁ የመሰረተ ልማቶች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ትግበራ ተከናውኗል።
ወቅታዊና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ዌብ ሳይት (website):https://www.aaitdb.gov.et ፌስቡክ (Facebook page):https://www.facebook.com/AAITDB
ኢሜይል (Email): aaitdb@aaca.gov.et
መስመር ስልክ (Phon Number):+251-118547714
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments